በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ለማስጀመር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ መምህራን ተመረቁ

0
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ለማስጀመር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ መምህራን ተመረቁ ............................................................................................................................................................................................................. ታህሳስ 06/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ለማስጀመር የአቅም ግንባታ ሥልጠና በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሲከታተሉ የነበሩ መምህራን አጋሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ 32 መምህራን ለ8 ወራት በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሜሪ ሉ ፉልተን መምህራን ኮሌጅ በInstructional Design and Performance Improvement ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ሲሆን በዕለቱ በግራጁዌት ሰርተፊኬት ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም በዕለቱ የዲጂታል ትምህርት አዘገጃጀት የአሰልጣኞች ስልጠናን በኮሌጁ ሲከታተሉ የቆዩ 19 መምህራንም ተመርቀዋል፡፡

Post a Comment

0Comments

Post a Comment (0)